Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዩጋንዳ ካማፓላ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በዩጋንዳ መዲና ካማፓላ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት አወገዘ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ÷በትናንትናው ዕለት በካምፓላ ሁለት ቦታዎች ላይ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት በንጹሃን ዜጎችና ፖሊስ ባልደረቦች ላይ በደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡
 
ኢትዮጵያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝም ነው በመግለጫው የተመላከተው ፡፡
 
ኢትዮጵያና ዩጋንዳ በጋራ ሽብርተኝነትን የመዋጋት ልምድ እንዳላቸው በመጥቀስ ጥቃቱ ዩጋንዳም ሆነ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሽብርተኝነትን የበለጠ በቁርጠኝነት ከመዋጋት እንደማያግዳቸው መጥቀሱን ከውጭ ጉዳዩ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለኡጋንዳ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.