Fana: At a Speed of Life!

የነቀምቴ ነዋሪዎች የአሸባሪዎችን ሴራ ለማክሸፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፈው የአሸባሪዎቹን ህወሓትና ሸኔን የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታወቁ።
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ በነቀምቴ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
 
በውይይቱ ወቅት ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት፥የአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ተላላኪዎች ወደ አካባቢያቸው ሰርገው እንዳይገቡ ከጎረቤታቸው ጋር በመደራጀት ነቅተው በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በተለይም ከጦርነቱ በላይ ያልተጨበጠ ወሬ ሕብረተሰቡን እያሸበረ በመሆኑ በመተባበር የጥፋት ሴራውን ለማክሸፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡
በየከተማው የውትድርና ሥልጠና ከወሰዱት ወጣቶች ጋር በመደራጀት በየአካባቢያቸው የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ከመከላከያ ጎን በመሰለፍ አገርን ለማዳን እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡
ህወሓትና ሸኔ ደም እያፈሰሱና የአርሶ አደሩን ምርት እያቃጠሉ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ይሞክራሉ ግን አይቻላቸውም ብለዋል፡፡
ወጣቱ ለጠላት የሀሰት ወሬ ጆሮ መስጠት እንደሌለበትና ተደራጅቶ የአካባቢውን ሠላም ከማረጋገጥ ባሻገር ወደ መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀል አገሩን ከአሸባሪዎች ማዳን አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የነቀምቴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ቶሌራ ረጋሳ፥ አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ አገርን ለማፈራረስ እየጣሩ መሆናቸውን ጠቁመው፥ ነዋሪው የአሸባሪዎችን ከንቱ ምኞት ለማክሸፍና ኢትዮጵያን ለማስቀጠል አንድነቱን አጠናክሮ በመደራጀት ድጋፉን መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.