Fana: At a Speed of Life!

በአገራችን ለተፈጠረው ጦርነት መንስኤውና ተጠያቂው አሻባሪው የህወሓት ቡድን ነው- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገራችን ውስጥ አሁን ለተፈጠረው ጦርነት መንስኤውና ተጠያቂው አሻባሪው የህወሓት ቡድን መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በሸራተን አዲስ ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል።

የጋራ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ ፥ ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ባለቤትና የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ቀንዲል መሆኗን የጠቀሰው የጋራ ምክር ቤቱ ፥ ዴሞክራሲያዊና የሰለጠነ ፖለቲካ ስርዓት እንዲፈጠር ለረጅም ጊዜ ሙከራዎችን ስታደርግ እንደነበርና ለዚህም በርካታ የህይወት መስዋትነት መከፈሉን አስታውሷል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው አሁን ለተፈጠረው ጦርነት መንስኤው አሻባሪው የህወሓት ቡድን መሆኑን ጠቅሶ ÷ ከ20 ዓመታት በላይ ተቀማጭነቱን ትግራይ ላይ ባደረገው የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የፈጸመው የክህደቱ ጥግ ማሳያ እንደሆነ አለም ሊገነዘብ ይገባል ብሏል።

አንድ ዓመት ያስቆጠረው ይህ ጦርነት እየሰፋ በመምጣቱና በተለይም በአማራና በአፋር ክልሎች ህዝቦች ላይ ከፍተኛ የሆነ ውድመት ማስከተሉንና ለዚህም ምክንያቱ የአሸባሪው ህወሓት የሀገር አፍራሽነት ጦረኝነት እንደሆነ መግለጫው አውስቷል።

የጋራ ምክር ቤቱ አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች፣ አለም አቀፍ ተቋማት፣ መንግስታትና ግለሰቦች የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በማዛባት እየተበተነች አስመስለው የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች የፖሮፖጋንዳ ጦርነት አካል መሆናቸውን ታዝቤያለሁ ብሏል።

ከህጋዊ መንግስት ውጭ የትኛውንም የአሻጉሊት መንግስት በህዝብ ላይ የመጫን ሀሳብ የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጹም እንደማይቀበልና የጋራ ምክር ቤቱም በጽኑ የሚያወግዘው መሆኑን በመግለጫው አሳስቧል።

የጋራ ምክር ቤቱ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች እና በሀገራችን ወቅታዊ ችግር ምክንያት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ፤ ህዝቡ ተደራጅቶ ሀገሩን ከውስጥና ከውጭ ጠላት እንዲጠብቅ ያሳሰበ ሲሆን ፥ በተለያዩ ቦታዎች አሸባሪው ሀይል ከመኖሪያ ቀያቸው ያፈናቀላቸውን ንጹሀን ዜጎች መንግስትና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቋል።

የጋራ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጠቀሜታ አድንቆ፣ አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግ ንጹሃን ዜጎችን እንዳይጎዳ በጥንቃቄ እንዲፈጸምና መንግስት የጀመረውን በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልበት መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.