ሀገርና ህዝብን ከምጊዜውም በላይ በቅንነት ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል አሉ የድሬዳዋ የመንግስት ሠራተኞች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየተሰማሩበት የሥራ መስክ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሀገርና ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን የድሬዳዋ የመንግስት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡
ሠራተኞቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከውይይቱ ተሳታፊ የመንግስት ሰራተኞች ፥ ሙያዊ ግዴታቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመወጣት ሀገርና ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን ነው ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት የተናገሩት፡፡
በህልውና ዘመቻው እየተዋደቀ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም መለገሳቸውን አውሰተው፤ ”በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን በገንዘብ፣ በአልባሳትና በምግብ ቁሶች መደገፌን እቀጥላለሁ” ብለዋል፡፡
የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ነው የገለጹት፡፡
አሸባሪዎቹ ወያኔና ሸኔ ተጣምረው ሀገር ለማፍረስ የሚያካሂዱትን ጦርነት ለመመከት ከሠራዊቱ ጎን በመሆን በግንባር ለመፋለም ጭምር መሆናቸውን ጭምር ገልጸዋል፡፡
”በደሞዜ፣ በጉልበቴ ፣ባለኝ ቁሶች ሁሉ የህልውናው ዘመቻ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ እተጋለሁ” ብለዋል፡፡
እያካሄድን ያለው ጦርነት ፍትሃዊና ሀገርን የማዳን ነው ያሉት ደግሞ አቶ በያን አደም ናቸው፡፡
የመንግስት ሠራተኞች በውይይታቸው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት፥ አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እየፈጠሩ ያሉትን ጫና ለመመከት ከምንጊዜውም በላይ ተቀናጅቶ መስራትና ሀገራችን ወደ ሰላምና ብልጽግና ማሻገር ይገባናል ነው ያሉት፡፡
የውይይት መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፤አስተዳደሩና ነዋሪው የሀገርን ህልውና ዘመቻው በስኬት እንዲጠናቀቅ በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!