Fana: At a Speed of Life!

ኢኮኖሚያዊ ጫናውን ለመቋቋም ሀገር በቀል አማራጮች ላይ ማተኮር ይገባል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ላይ ተጠናክሮ የቀጠለውን ጫና ለመቋቋም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ አማራጮች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ምሁራን ገለጹ፡፡
 
በአየርላንድ ዩኒቨርሲቲ የ3ተኛ ዲግሪ ተማሪና የማህበራዊ ሳይንስና የፖለቲካ ተንታኙ አቶ ንጋቱ አበበ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ውስጥ የሚልኩትን የውጭ ምንዛሬ እንዲያሳድጉ ማድረግ አንዱ አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ሃይሉ ነጋ በበኩላቸው÷የአሜሪካንን የአፍሪካ ቀንድ ሴራ አስፈጻሚ የነበረውን ሃይል ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት በህብረት ማክሸፍ ደግሞ ሌላኛው ጫናው የመቋቋሚያ መንገድ መሆኑ አስረድተዋል፡፡
 
የማዕቀብና የድጋፍ ማቋረጥ የምዕራቡ አለም ጫና መቋቋሚያ አማራጩ ግን መፍትሄው የሚጀምረው አሸባሪ ቡድኑን የመቅበር ስራው ከቀደመ ብቻ ነው ብለዋል።
 
ወደ ሀገር ውስጥ የሚልኳቸው ገንዘቦች በህጋዊ መንገድ ማድረግ ደግሞ የኢኮኖሚ ማዕቀብና ድጋፎች መቋረጥን ለመመከት አቅም እንደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡
 
የህዝባዊ አንድነቱ ሊጠናከር እንደሚገባውና መሰል ጫናዎችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት ምህራኑ።
 
በሃይለየሱስ መኮንን
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.