Fana: At a Speed of Life!

“ትልቁ ጉዳይ አገራችን” የተሰኘ የባለሀብቶች ኮሚቴ ለወገን ጦር ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መሠረቱን ወሎ ያደረገው “ትልቁ ጉዳይ አገራችን” የተሰኘ የባለሃብቶች ኮሚቴ በወሎ ግንባር ሽብርተኛውን ህወሓት እየደመሰሰ ለሚገኘው የወገን ጦር ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉን ያስረከቡት የኮሚቴው ሰብሳቢ ቤንቤላ አብዱልቃድር በዚህ ወቅት ከምንም በላይ የሐሳብ አንድነት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የህልውና ዘመቻውን እንዲደግፍም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የባለሃብቶቹ ቡድን ከ4 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቴምር፣ ብስኩት እና ሌሎች ድጋፎችን ያካተተ መሆኑን አስታውቀዋል።
ባለሃብቶቹ ወደፊትም የተጠናከረ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ነው ቃል የገቡት፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግንባሩ የሎጂስቲክስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋ ዳኘው÷ ወሎን የወረረውን ሽብርተኛው ህወሓት ለመደምሰስ እየተደረገ ባለው ትግል የአካባቢው ባለሃብቶች ጠንካራ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የወሎና አካባቢው ባለሃብቶች ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያው አለመሆኑንም አስታውቀዋል።
 
አሸባሪው ህወሓት ከምድረ ገጽ እስኪጠፋ ሁሉም ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውንም አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.