Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ የሰላም ግንባታ ስራዎችን መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎችን በቀጣይነት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ከጀርመኑ ተራድኦ ድርጅት (ጂ አይ ዜድ) ጋር ተፈራረመ።
 
ሰነዱ የተፈረመው ስራዎቹ ላለፉት ሶስት አመታት እየተከናወኑ የነበሩና በሁለቱም ወገን አስፈላጊነታቸው በመታመኑ እንዲቀጥሉ ስምምነት ላይ በመደረሱ ነው ተብሏል።
 
የመግባቢያ ስምምነቱን በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደአና የጂ አይ ዜድ የኢትዮጵያና ጂቡቲ ተወካይ የሆኑት ፒተር ፓለሽ ተፈራርመውታል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጀርመን መንግስት በጂ አይ ዜድ በኩል እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና ማቅረቡን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.