በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የሚሹ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ ጎን መቆም አለባቸው-አምባሳደር ነቢል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓትን በማስወገድ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የሚሹ የአፍሪካ አገራት ከኢትዮጵያ ጎን መቆም እንዳለባቸው በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ አሳሰቡ።
አምባሳደር ነቢል ከሱዳን ፖስት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት አሸባሪው ህወሓት ባለፈው ሰኔ ሰብአዊነትን ባስቀደመ ውሳኔ መከላከያ ከትግራይ ክልልን ለቆ መውጣቱን እንደመልካም አጋጣሚ በመወሰድ በአጎራባች የአፋርና የአማራ ክልሎች ላይ ወረራ በመፈጸም ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን እያደረሰ ነው።
በመሆኑ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የሚሹ የአፍሪካ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
ቡድኑ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀ በመሆኑ የድርጅቱን የጥፋት አድማስ ለማጥበብና አመራሮቹንም ለህግ ለማቅረብ የአፍሪካ ሃገራት ከኢትዮጵያ ጋር እንዲተባበሩም ጠይቀዋል።
“በዚህ ፈታኝ ወቅት የአፍሪካ አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር በአንድነት መቆም አለባቸው፣ የአፍሪካ አገራት በምዕራቡ ዓለም የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ግራ ሊጋቡ አይገባም” ብለዋል፡፡
በአፍሪካ ብቸኛዋ ነፃ አገር በሆነችው በኢትዮጵያ በኩል አፍሪካን አዲስ ቅኝ ግዛት ለመግዛት የምዕራባውያን አገሮች ድብቅ አጀንዳ አላቸው ሲሉም ከሰዋል።
አምባሳደሩ አሸባሪ ድርጅቱን በህዝብ ምርጫ ወደ ስልጣን ከመጣው ህጋዊ የኢትዮጵያ መንግስት ጋር እኩል ደረጃ ለማስቀመጥ የሚደረገው ሙከራ በፍጹም ተቀባይነት የለውም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አሸባሪ ቡድኑ ዳግመኛ ወደ ስልጣኑ ቢመለስ የመጀመሪያዎቹ የአለመረጋጋትና ቀጠናዊ ምስቅልቅል ገፈት ቀማሾች የኢትዮጵያና አጎራባች አገራት በመሆናቸው ለኢትዮጵያ የሚያደርጉት ሁለንተናዊ እገዛ የሰላምና መረጋጋታቸው ዋስትና መሆኑንም አስምረውበታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!