ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በካናዳ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጠራው ‘#NOMORE’ ዘመቻ ሰልፍ በካናዳ ኦቶዋ ተካሄደ፡፡
በሰልፉ ላይ በካናዳ ኦቶዋ፣ ቶሮንቶ፣ ሞንትሪያል፣ ኩቤክ፣ ስካርብሮ፣ ኪንግስተን እና ሌሎች ከተሞች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትና የኤርትራ ዜጎች ተሳትፈዋል፡፡
የምዕራባውያን ሃገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና የሚያወግዙ፤ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ላይ እየሰሩ ያሉትን ግጭት አባባሽ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲያቆሙ ጥሪ የሚያደርጉ መልዕክቶች በሰልፉ ላይ ተላልፈዋል፡፡
ለካናዳ ፓርላማ እና በኦቶዋ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚያስገነዝብ ደብዳቤ እንደሚሰጥም ተገልጿል።
ሰልፉ ዛሬ የምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና በመቃወም በመላው አለም በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሚከናወነው ሰልፍ አካል መሆኑን ከዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን