Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጉጂ ዞን ህብረተሰቡ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሰ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጉጂ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል።

በምዕራብ ጉጂ ዞን የቡሌ ሆራ ከተማ ደም ባንክ ማዕከል ማስተባበሪያ እንደገለጸው ÷ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም የለገሱት ሴቶች፣ ወጣቶችና እናቶች ናቸው።

ደም የለገሱት በጎ ፈቃደኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ በኋላ ደጀንነት የሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍና ትብብር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የደም ባንክ ማዕከሉ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሀብታሙ ኃይሉ ÷ በግል ፍላጎትና ተነሳሽነት ደም የለገሱት 63 በጎ ፈቃደኛ ሴት ወጣቶችና እናቶች ብቻ እንደሆኑ አስታውቀዋል፡፡

ከምዕራብ ጉጂና ቦረና ዞኖች ከበጎ ፈቃደኞች ደም የሚያሰባስቡ 34 የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች መሰማራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዞኖቹ ሞያሌ፣ ቡሌ ሆራ፣ ያቤሎ ተልተሌ፣ አባያና መልካ ሶዳ ከተሞችና ወረዳዎች ከበጎ ፈቃደኞች 3ሺህ ዩኒት ደም ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ሽብርተኛው ህወሓት በንጹሀን ላይ ያደረሰው ጥቃት በፈጠረው መነሳሳት ባለፉት ሶስት ወራት በ85 በጎ ፈቃደኞች 85 ዩኒት ደም መለገሱን አስታውሰዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.