የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በሀገር ላይ የተከፈተን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ለመቀልበስ መስራት አለባቸው – ምሁራን
አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የምዕራቡ ዓለም በሀገር ላይ የከፈቱትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ለመቀልበስ በትጋት መስራት አለባቸው ሲሉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ።
የምዕራቡ ዓለም የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ እያካሄዱት ላለው ከእውነት ያፈነገጠ የመገናኛ ብዙሀን ዘመቻ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ምሁራኑ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካና ምዕራባውያን ኢትዮጵያን ለማዳከም አልመው መነሳታቸውን በመገናኛ ብዙሀኖቻቸው ከሚያሰራጯቸው ዘገባዎችና ከሚያንጸባርቁት አቋም ኢትዮጵያውያን እየተረዱ መምጣታቸውንም ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምህር ዶክተር ጌታቸው ጥላሁን እንዳሉት፥ ኢትዮጵያዊያን የምእራባዊያንን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ የምንቀለብስበት ዋነኛው መሳሪያ እውነታውን የሚያሳይ ዘገባ በተደራጀና በታቀደ መልኩ በመስራት ነው፡፡
“በኢትዮጵያ ውስጥ በትክከል እየሆነ ያለውን ሳይሆን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ መርጠው ለሚዘግቡ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን፣ በእውነት ላይ የተመሰረተ ዜና ሰርቶ በማሳየት ታአማኒነታቸውን ማሳጣት ይቻላል” ብለዋል፡፡
ይህን ተከታትሎ ለማስተካከል ዓለምአቀፍ ወቅታዊ ሁኔታዎችን የቃኘ የመረጃ አደረጃጀትና ስርጭት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ መምህሩ ዶክተር ደመላሽ መንግስቱ በበኩላቸው ፥ “የዓለምአቀፉ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ጉዳይ ከግንባሩ ጦርነት ባልተናነሰ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል” ነው ያሉት፡፡
“ከሺህ ጦረኛ አንድ ወረኛ” እንደሚባለው “የሚናፈሰው ሀሰተኛ የዜና ሽፋን ሲደጋገም ተጽዕኖ መፍጠሩ ስለማይቀር ሀሰተኛ ዘገባ በማሰራጨት ላይ የተጠመዱ መገናኛ ብዙሀንን እየተከታተሉ ሀሰተኛነታቸውን ለዓለም ማሳየት የግድ ይላል” ብላዋል መምህሩ፡፡
የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን ከተለመደው አሰራር ወጥተው አሁን ያለውን አድማጭ የሚመጥኑ አሳማኝ መረጃዎችን በማዘጋጀት በኩል የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን ሌት ተቀን እንዲሰሩ ጠቁመዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!