ማንኛውንም የጥፋት ቡድን ለመከላከል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንገኛለን-የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉን ሠላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀስን ማንኛውንም የጥፋት ቡድን ለመከላከል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ከሰሞኑ በክልሉ የአሸባሪ ቡድኑን ተልዕኮ ተቀብለው በሱዳን በኩል የገቡ ኃይሎችን የተደመሰሱ ሲሆን÷ የተቀሩት ደግሞ ሸሽተው መመለሳቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም ሙሃመድ እንደገለጹት÷ ሀገር ለማፍረስ የሚቀሳቀሰውን የህወሃት አሸባሪ ቡድን ተልዕኮ ተቀብለው የክልሉን ሠላም ለማደፍረስ የውስጥና የዉጪ ቅጥረኞች እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
እነዚህ ቅጥረኞች ከአሸባሪ ቡድኑ በሚሰጣቸው ድጋፍ በክልሉ ካማሺና መተከል ዞኖች የጥፋት ተግባራትን እየፈጸሙ እንደሚገኝ ጠቅሰው÷ የጥፋት ቡድኖቹ ባልተለመደ የጦር መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ጥፋት እየፈፅሙ ቢሆንም በክልሉ የጸጥታ ኃይል እየተመከተ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ቀደም ሲል የጥፋት ቡድኑ ተላላኪዎች በከማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የያዙትን የጥፋት ሴራ ሙሉ ለሙሉ በማክሼፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነፃ መደረጉንጠቁመዋል፡፡
አሁንም በሌሎች አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ኃይሎችን በማስወገድ የክልሉን ሠላም ለማረጋገጥ የክልሉ የጸጥታ ኃይል በሙሉ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ነው የገለጹት፡፡
ከውስጥ ባንዳዎች ባሻገር በአጎራባች ሱዳን በኩል በሽብር ቡድኑ ስልጠናና ተልዕኮ ወስደው ወደ ክልሉ ገብተዉ ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክሩ አካላትን በጥንቃቄ በመከታተል ተልዕኳቸውን ማክሸፍ መቻሉንም ኮሚሽነር አብዱልአዚም ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ በሱዳን በኩል ሰርገዉ በመግባት ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥቃት ለመፈፀም የተንቀሳቀሱ 200 የጥፋት ኃይሎችን ሙሉ በሙሉ በማጥቃትና በመደምሰስ የጥፋት ዓላማቸውን ማክሸፍ መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የጥፋት ቡድኑ ከያዛቸው የተለያዩ የጦር መሳሪዎች መካከል 7 ፈንጂዎች ውስጥ አንዱን ለማፈንዳት ቢሞክርም የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ባደረገው ውጊያ ምንም ጉዳት ሳያደርስ ቀሪ 6 ፈንጆችና ሌሎች መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን አብራርተዋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስፈላጊውን የሰዉ ኃይልና የመሳሪያ ዝግጅት በማድረግ በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ አንደሚገኝ ም አረጋግጠዋል፡፡
ህብረተሰቡም በተለያዩ ስራዎች ተሰማርተው የጁንታውን ተልዕኮ ለማስፈፀም የሚሞክሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ለክልሉ ሠላም መረጋገጥ ከጎናቸው እንዲቆም መጠየቃቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
ካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!