Fana: At a Speed of Life!

ከ110 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቃዮች ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከ110 ሚሊየን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ለሰራዊቱና ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ ሰራተኞች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ደማቸውን ለግሰዋል፡፡

ሰራተኞቹ “ደማችንን በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊታችን ደጀን መሆናችንን እናረጋግጣለን” በሚል መርህ ነው ደማቸውን የለገሱት፡፡

በደም ልገሳው የተሳተፉ ሰራተኞች #no_more (በቃ) በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራብያውያን አገራትና የመገናኛ ብዙሃኖቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና አውግዘዋል፡፡

የኮሚሽኑ ሰራተኞች የአገርን አንድነት ለማስጠበቅ እየተዋጋ ላለው ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ደም የለገሱት፡፡

በቀጣይ ቀናት ሁሉም የኮሚሽኑ የማዕከልና በዘጠኙም ቅርንጫፎች የሚገኙ ሰራተኞች የሚለግሱ መሆኑ ታውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ሰራተኞች በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.