Fana: At a Speed of Life!

የአገርን ክብር ሊደፍሩ ያሰፈሰፉ ጠላቶችን በመቅጣት የአድዋን ታሪክ ዳግም እንጽፋለን-አቶ ግርማ የሺጥላ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገርን ክብር ሊደፍሩ ያሰፈሰፉ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የአድዋን ታሪክ ዳግም እንጽፋለን አሉ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ፡፡
አቶ ግርማ ጉዳዩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የዳግማዊ አድዋን ታሪክ የምንፅፍበት ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ነን ያለጥርጥር ደማቅ ታሪክም እንፅፋለን ብለዋል፡፡
የአገርን ክብር ሊደፍሩ ያሰፈሰፉ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተን የአድዋን ታሪክ ዳግም እንፅፈዋለንም ነው ያሉት፡፡
የአማራ ህዝብም ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር ሁኖ መሪወቹን ይከተላል፤ በወንድማማችነትና በጋራ መስዋዕትነት ኢትዮጵያን ያፀናል ብለዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.