Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ለመከላከያ ሰራዊት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት 13 ሺህ 806 ብርድ ልብስ እና 5 ሺህ አንሶላ ለመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በድጋፉ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ ኮሎኔል ተመስገን አስማማው÷ ድጋፍ ያደረግነው ሁሌ ከሰራዊታችን ጎን መሆናችንን ለማሰያት ነው ብለዋል ፡፡

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ የመደኃኒት መገልገያ ህክምና መሳሪያ አቅርቦት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴር ጄኔራል የሺእመቤት አስማማው በበኩላቸው÷ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለመከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች 594 ሺህ 590 ብር በማሰባሰብ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ማበርከቱን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.