Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መተዳደሪያ ህገ መንግስቱን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መተዳደሪያ ህገ መንግስቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመስርቷል፡፡
 
ምስረታው ከአምስቱ ዞኖችና ከአንድ ልዩ ወረዳ የተወከሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በቦንጋ ከተማ የተካሄደው፡፡
 
በዚህም አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት መተዳደሪያ ህገ መንግስቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
 
በተጨማሪም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የስራ ቋንቋ አማርኛ እንዲሆንበሙሉ ድምጽ የጸደቀ ሲሆን÷የዞን መዋቅሮች ደግሞ የራሳቸውን ቋንቋ እንደሚገለገሉ ተገልጿል።
 
 
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.