በሲዳማ ክልል ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ሽኝት ተደረገላቸው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል አገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ግንባር ለመዝመት ፍቃደኛ የሆኑ የቀድሞ ሰራዊት አመራሮች ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አባላት በዛሬው እለት በሀዋሳ ከተማ ሽኝት ተደረገላቸው።
በሽኝት ዝግጅቱ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም በማለት በአንድ ላይ የተነሳበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ኢትዮጵያም አሸንፋ እንጂ ተሸንፋ አታውቅም ብለዋል።
ለመዝመት የወሰናችሁ ሁላችሁም ባላችሁ ልምድና እውቀት ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ማድረግ አለባችሁ ሲሉም ተናግረዋል።
በአገር ደረጃ በተከፈተው ጦርነት ላይ ክልሉ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ያሉት ደግሞ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ክልሉ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሰራዊት መልምሎ ወደ ግንባር ከመላክ ባሻገር በተለያዩ ግንባሮች የራሱን የሰራዊት አባላት በመላክ በውጊያው ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል።
ከፍተኛ የጦርነት ሙያ ያላቸውና አመራሮችና መኮንኖች እንዲሁም የሽምቅ ውጊያን ለረጅም አመታት የመሩና ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ እንደሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ወጣቶችም በሰራዊት ምልመላ ላይ በንቃት እንዲሳተፋና አገራቸውን እንዲጠብቁ በማለትም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የክልሉ ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ በረከት ኪኤ እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ሁልጊዜም ቢሆን አገራችንን ከጠላቶቿ እንጠብቃታለን ብለዋል።
በብርሃኑ በጋሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!