Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ቴድሮስ ተሾመ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀሉን አሰታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ቴድሮስ ተሾመ የህልውና ዘመቻውን መቀላቀሉን “የኔ ማለፍ ሀገሬን የሚያቆያት ከሆነ ለመሠዋት ዝግጁ ነኝ” ሲል አስታውቋል።
 
አርቲስት ቴድሮስ ተሾመ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልእክት÷ “ሀገራችን ከምን ጊዜውም በላይ ትፈልገናለች ብሏል፡፡
 
አሁን ትግሉ ከኮምፒውተሩና ስልኩ አልፎ በአካል ሊሆን ግድ ብሏል፤ መተኮስ እችላለሁ። የኔ ማለፍ ሀገሬን የሚያቆያት ከሆነ ለመሠዋትም ጭምር ዝግጁ ነኝ ነው ያለው፡፡
 
ኢትዮጵያዊ ከሆንክ፣ ሙሉ የአካል ብቃት ካለህ፣ ይህ እድል እንዳያመልጥህ! ና በጋራ ሀገር እናኑር! በዚህ ወቅት አንተ ሙሉ ብቃቱ እያለህ ለሐገርህ ዘብ ለመሆን ካመነታህ ነገ በልጆችህ ፊት ታሪክ ሲወቅስህ ትሸማቀቃለህ!!
 
እህቴ መልእክቱ ላንቺም ጭምር ነው፤ትግል ሜዳ እንገናኝ ፤ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!” ሲል ጥሪውን አስተላልፏል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.