Fana: At a Speed of Life!

ወቅቱ የክልሉ አርሶ አደር የሀገር ዋልታ መሆኑን በሁለት ግንባር የሚያሳይበት ነው – የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ አርሶ አደር የሀገር ዋልታ መሆኑን በሁለት ግንባር የሚያሣይበት ጊዜ ላይ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሃይለማርያም ከፍያለው ገለጹ፡፡

ሃላፊው አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ ክልል ወረራ ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ የክልሉ ህዝብ በህልውና ዘመቻው ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም አርሶ አደሩ ያደረገው ተጋድሎ ቀላል አለመሆኑን ነው ዶክተር ሃይለማርያም የገለጹት፡፡

አሸባሪው ወረራ ባደረገባቸው የክልሉ ዞኖች አርሶ አደሮችን ገድሏል ፤ በሠብላቸው እና እንሰሳት ላይ ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል፡፡

ድህነትን እና የህወሓት እኩይ ሴራን የማፍረስ ድርጊትን በቀዳሚነት ልንዋጋቸው የሚገባቸው ጉዳዮች እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡

አርሶ አደሩም ከልማት ስራው ባሻገር በሙሉ ወኔ እንዲታገልና ልጆቹን ለሃገር ማዳን ጥሪ መርቆ እንዲሸኝ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በረሃብና ድህነት ላይ በሚደረግ ዘመቻም ወራሪ ሃይሉ ጋር በሚደረገው ትግል አካባቢዎች ውጭ የሚገኙ የክልሉ አርሶ አደሮች የመኸር ምርትን ያለ ብክነት መሠብሰብና የቁጠባ ባህልን ማዳበር እዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ከምንም በላይ በክልሉ ወራሪ ሃይሉ ጉዳት ባደረሰባቸው 6 ዞኖች ውስጥ የተከሰተውን የምርት ውድመት ለማካካስ በዳግም እርሻና በመስኖ መርሃ ግብር የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም በእጥፍ ማምረት እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

ለእነዚህ የግብርና ተግባራት ስኬታማነት የአፈር የውሃ እና የሠብል ምርምር ተቋማት ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች እና ከክልል እስከ ቀበሌ የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች በተቀናጀና በትብብር ከአርሶ አደሩ ጋር ይሰራሉ ፤ መሥራትም አለባቸው ነው ያሉት፡፡

በአለባቸው አባተ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.