Fana: At a Speed of Life!

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት የ82 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊት 82 ሚሊዮን ብር የሚገመት የጥሬ ገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል።
 
ክፍለ ከተማው 32 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ እና 50 ሚሊየን ብር በዓይነት መስጠቱን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀሚል ረዲ ተናግረዋል።
 
በዓይነት የተደረጉት ድጋፎች 250 በሬዎች እና 640 በጎች ሲሆኑ ግምታቸው 50 ሚሊየን እንደሆነ ተገልጿል።
 
ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ስራ አስፈፃሚው በርክክቡ ወቅት መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስቴር ፋውዴሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ኮሎኔል አማን ገነሞ በበኩላቸው÷ የተደረገው ድጋፍ ለሰራዊቱ የምራል ስንቅ እንደሚሆነው ተናግረዋል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.