የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት በ2ኛ ቀን ውሎው የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
ምክር ቤቱ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የቀረቡ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችን ሹመት አጽድቋል።
በዚህ መሰረት፡-
1ኛ. አቶ ጸጋዬ ማሞ – የመንግሥት ዋና ተጠሪ
2ኛ. አቶ ማስረሻ በላቸው – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርና ቢሮ ኃላፊ
3ኛ. አቶ አልማው ዘውዴ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
4ኛ. አቶ ሳጂዮ ሳፒ – በመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
5ኛ. አቶ ተዘራ ወልደማርያም – ረዳት የመንግስት ተጠሪ በመሆን የፖለቲካ እና የርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ
6ኛ. አቶ በላይ ተሰማ – የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሆነው የአደረጃጀት ዘርፍ እንዲመሩ ተሹመዋል።
ከዚህ ባለፈም ምክር ቤቱ የካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን :-
1. ኢንጂነር የማታዓለም ቸኮል – የከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. ወይዘሮ ወሠነች ቶማስ – የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3. ወይዘሮ ፋንታሁን ብላቴ – የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ አንድነት አሸናፊ – የሠላም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ አሰፋ ጊንዶ – አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ ተክሌ በዛብህ – የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ተመስገን ከበደ – የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
8. ኢንጂነር በየነ በላቸው – የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
9. አቶ ተስፋዬ እንዳሻው – የክህሎት እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
10. አቶ ኢብራሂም ተማሚ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
11. ወይዘሮ ገነት መኩሪያ – የሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ግዛው ጋጊያ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
13. አቶ የሺዋስ ዓለሙ – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
14. ወይዘሮ ሕይወት አሰግድ – የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
15. አቶ አስራት ሀዳሮ – ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
16. ዶክተር ኢንጂነር አስራት ገብረማርያም – የደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ለውጥ ቢሮ ኃላፊ
17. ወይዘሮ ቤተልሔም ልዑል – የኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በሙሉ ድምጽ መሾማቸውን ከደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!