Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ያደረጉት ኢትዮጵያ የአፍሪካ የትግል ማዕከል ስለሆነች ነው – ኡጋንዳዊው ፓን አፍሪካኒስት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራባውያኑ በኢትዮጵያ ላይ ትኩረት ያደረጉት ኢትዮጵያ የአፍሪካን የጸረ ቅኝ ግዛትና የጸረ ኢምፔሪያሊስት ትግል ማዕከል በመሆኗ ነው ሲሉ ኡጋንዳዊው ፓን አፍሪካኒስት ማቱ ጆብ ሪቻርድ ተናገሩ።

ፓን አፍሪካኒስት ማቱ ጆብ ሪቻርድ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ አፍሪካውያን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከኢትዮጵያ ጎን መቆም አለባቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትዋጋው ጦርነት ቀላልና መደበኛ ጦርነት ሳይሆን አፍሪካን ሊቀይር የሚችል የአፍሪካን ጦርነት እንደምትዋጋ ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ የምትገኝበት አካባቢ በርካታ የተፈጥሮ ሃብት የሚገኝበት መሆኑን ገልጸው ይህንንም የተፈጥሮ ኃብት ምዕራባውያኑ በቅጡ ያውቁታል ብለዋል።

ስለዚህም ምዕራባውያኑ ይህንን የተፈጥሮ ኃብት መቀራመት የሚችሉት ኢትዮጵያንና አካባቢውን ማተራመስ ሲችሉ ብቻ መሆኑን ገልጾ ÷ ይህንንም በቅጡ መገንዘብ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።

በሌላ በኩል በምዕራባውያኑና በምስራቁ ዓለም መካከል ያለው ፍጥጫ በግልጽ እየታየ መሆኑን ገልጸው ÷ በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት የውክልና ጦርነት መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም የአሜሪካና የአንዳንድ ምዕራባውያን አገራት ጥምረት ቻይና አሁን በአፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለማኮላሸት ያለመ መሆኑንም ገልጸዋል።

አሜሪካና ሌሎች የምዕራባውያን አገራት ወደ አፍሪካ የሚመጡት በሰብዓዊ መብትና በዴሞክራሲ መሆኑን ጠቁመው ÷ ነገር ግን እነዚህ አገራት ለሚሉት ነገር ታማኝ አለመሆናቸውን አንስተዋል።

ለአብነትም አሜሪካውያኖች በጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊያኖች ላይ የሰሩትን ግፍና በዴሞክራሲ ስም ሊቢያ መፈራረሷን ጠቅሰው ÷ አፍሪካዊያን ሊነቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡን ለማነሳሳት ኢትዮጵያን የተመለከቱ በርካታ ፕሮፓጋንዳና የሃሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም የአፍሪካ አገራት ኢትዮጵያን መደገፍ አለባቸው ፤ የፓን አፍሪካኒስት አቀንቃኝ የሆኑ ዩጋንዳውያንም ይህንን በተግባር አሳይተዋል ብለዋል።

እርሳቸውና ሌሎች የአፍሪካ ወዳጅ አገራት ዜጎች አሁን ኢትዮጵያ ላይ የሚካሄደውን የሃሰት ዘመቻ በጥንቃቄ እየተከታተሉና እየተከላከሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.