የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፋሪስ ደሊል፥ ዩኒቨርሲቲው ቀደም ብሎ ግንባር ድረስ በመገኘት ሰራዊቱን ከማበረታታት ባሻገር የተለያዩ ቁሳዊ ድጋፎች ማድረጉን ተናግረዋል።
ለ4ኛ ጊዜ ባደረገው ድጋፍ በገንዘብ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ እና በአይነት 100 በሬ እና 120 ኩንታል ስኳር ድጋፍ ማድረጉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል ፡፡
ጀግናው የመከላከያ ሃይላችን በግንባር እየተዋደቀ አገርን ከሚያፈርሱ የሽብር ሃይሎች ጋር የሚያደርገውን አኩሪ ተግባር በመደገፍ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የፌዴራል ክልሎች ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ ፥የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሕወሓትን አገር የማፍረስ ተግባር በመቃወም በግንባር ለሚገኘው ለጀግናው የመከላከያ ሃይላችን ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!