Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሀሰን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በሃገሪቱ 11ኛ ክልል ሆኖ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች 11ኛ ክልል ሆኖ መመስረቱ የህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ መብት በለውጡ መንግሥት ተግባራዊ ምላሽ ማግኘቱ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

የፌዴራል ስርዓቱን መሠረት አድርገው የሚቀርቡ የህዝብ ጥያቄዎችን በወቅቱ ምላሽ መስጠት፣ ሃገሪቱ በለውጥ ሂደት ስለመሆኗ ማረጋገጫ መሆኑንም አቶ አሻድሊ ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ-መስተዳድሩ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ስታቀርቡት የነበረው የዓመታት ጥያቄ ፍፁም ሠላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ምላሽ በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.