Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት የዘር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 የምርት ዘመን ሀገራዊ የበጋ የስንዴ መስኖ ልማት ይፋዊ የዘር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በጋሞ ዞን የጋሞ ልማት ማህበር አርባ ምንጭ የእርሻ ልማት ላይ እየተካሄደ ነው።

ሀገራዊ የበጋ ስንዴ ልማት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ አካባቢዎች ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን÷ እንደ ሀገር 400 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ በስንዴ እንደሚለማ ተጠቁሟል።

በምርት ዘመኑ በሀገር አቀፍ 400 ሺህ ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ በስንዴ በማልማት 16 ሚሊየን ኩንታል ይገኛል ተብሎ መታቀዱም ተገልጿል።

በሀገራዊ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የዘር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የግብርና ሚንስትር ዴኤታ እና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር መለሰ መኮንን ፣በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የገጠር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር፣የፌደራል ፣የክልል እና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎችና አርሶ አደሮች ተሳታፊ ናቸው።

ሀገራዊ የበጋ መስኖ ስንዴ ይፋዊ የዘር ማስጀመሪያ ሂደትን በተዘጋጀው የእርሻ ቦታ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዶች በጋራ ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.