Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አመራሮች ወደ ግንባር ለመዝመት ወሰኑ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የመከላከያ ሠራዊትን በግንባር መምራት መጀመራቸውን ተከትሎ ሠራዊቱን ለመቀላቀል የሚመዘገቡ ዜጎች ቁጥር መጨመሩን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።
 
የዞኑ አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሐመድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥በዞኑ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በርካታ ሠዎች የሀገር የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
ከዚህም በተጨማሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አርአያ በመከተል የዞንና የወረዳ አመራሮች ወደ ግንባር ለመዝመት መወሰናቸውን ነው የገለጹት።
 
ዞኑ የህልውና ዘመቻውን ለሚቀላቀሉ አመራሮችና ሠራተኞችም አስፈላጊውን ሁኔታ ያመቻቻል ነው ያሉት፡፡
 
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን 134 ሚሊየን ብርን ጨምሮ 430 ሰንጋዎችና 470 ፍየሎችን ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁም ተመላክቷል፡፡
 
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.