በጅማ ዞን የማና ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ከ18 ሚሊየን ብር በላይ አሰባሰቡ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን የማና ወረዳ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት 18 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ማሰባሰባቸው ተገለፀ።
የወረዳው ነዋሪዎች ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ 23 ሰንጋዎች፣ 800 ኩንታል እህልና ቡና ለሰራዊቱ ድጋፍ ማድረጋቸውን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ፈድሉ ዛኪር ተናግረዋል።
ከድጋፉ ውስጥ 4 ሚሊየን ብርና 18 ሰንጋዎች የወረዳው ቄሮና ቀሬዎች ለሰራዊቱ የለገሱት ድጋፍ መሆኑን አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የወረዳው ነዋሪዎችና ወጣቶችም፥ ልጆቻቸውና ጓደኞቻቸው የህልውና ዘመቻውን መቀላቀላቸውን ጠቅሰው እነሱም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንባር ድረስ ወርደው ለአገር የሚከፈል ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ በተግባር አሳይተውናል ያሉት ወጣቶቹና ነዋሪዎቹ፥ መስዋዕትነት ከፍለው ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ እናስተልፋለን ብለዋል።
በሙክታር ጠሃ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!