Fana: At a Speed of Life!

እኔም እንደ መሪዬ እዘምታለሁ ላሉ የአራዳ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ አስተዳደር አፈ ጉባኤ ቡዜና አልካድር ዘማቾች የዚህ ህዝብ አካል በመሆን ታሪክ የማይረሳውናታሪክ ሰሪ ትውልድ ናችሁ ብለዋል፡፡
እኛ እያለን ሀገር ማፍረስ የማይሞከር ነው ያሉት አፈ ጉባዔዋ÷ ከአባቶቻችን በነፃነት የተረከብናትን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ በመወሰን ከሰራዊቱ ጎን ለመሰለፍ በመወሰናችሁ ክብር ይገባችኋል ብለዋል፡፡
በቅርቡም ጠላቶቻችንን በመቅበር በድል እንደምንገናኝ አልጠራጠርም ነው ያሉት፡፡
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር ተወካይ ብ/ጄ አስፋው ማመጫ በበኩላቸው÷ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር በዘመቱበት ማግስት የአዲስ አበባ ወጣቶች ወደ ሰራዊታችን ለመቀላቀል በመቻላችሁ ክብር ይገባችኋል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንባ በመሆን አመራር ለመስጠት መሰለፋቸው ከፍተኛ መነሳሳት ስለፈጠረባቸው ለመዝመት መወሰናቸውን የተናገሩት የአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ ስድስት አመራሮች ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን የጁንታውና ተባባሪዎቹን ሴራ ለመከላከል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.