Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላም እያበረከተችው ያለው አስተዋጽኦ ለመላው አፍሪካ ትልቅ ኩራት ነው – የጋና ወታደራዊ ልዑክ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለአለም ሰላም እያበረከተችው ያለው አስተዋጽኦ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካም ጭምር ትልቅ ኩራት ነው ሲሉ የጋና ወታደራዊ ልዑክ ገለፁ።

ልዑኩ በአብዬ የሚገኘውን የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የግዳጅ አፈፃፀም ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

የልዑኩ መሪ ኮ/ል ፍራንስስ ሳክ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ÷ ምንም እንኳን ጋና በሰላም ማስከበር ተሳትፎ ውስጥ የቆየች ሀገር ብትሆንም ኢትዮጵያ ደግሞ ከጋና በተሻለ ልምድ ያላትና በመንግስታቱ ድርጅትም እውቅናና አድናቆት የተቸራት አገር ናት ብለዋል።

እኛም ያየነው ይህንን ልምዷን ተጠቅማ በቀጠናው ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ በሁለቱ ሱዳኖች ስምምነት መሠረት በብቸኝነት ገብታ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በሚገባ ማረጋገጥ መቻሏን ነው ብለዋል።

ይሄ ደግሞ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካም ጭምር ኩራት መሆኑን ገልፀዋል።

የሻለቃው የሠራዊት አባላትም በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ግጭት እንዳይፈጠር እና ተቻችለው በሰላም እንዲኖሩ የሚያደርጉትን ፈታኝና እልህ አስጨራሽ ግዳጅ ፣ ከተደረገልን ገለፃ በተጨማሪ ተዘዋውረን በመጎብኘት ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል።

በጉብኝታቸውም ብዙ ልምድና ተሞክሮዎች ማግኘታቸውን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.