Fana: At a Speed of Life!

በመተግበሪያው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ በአሸባሪው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው በ’eyezonethiopia.com’ መተግበሪያ አማካኝነት በሃገር ቤት በአሸባሪው ህወሓት ባደረው ወረራ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር በላይ ደርሷል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ባለማውና ባስተዋወቀው እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ባመቻቸው መተግበሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።

ይህም ዳያስፖራው ምቹ ሁኔታ እስከተፈጠረለት ድረስ ሃገሩን ለመርዳት ያለውን ዝግጁነትና ዕምቅ አቅሙን አሳይቷል።

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናውን አቅርቧል።

ዳያስፖራውም ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል የአገር አለኝታነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥ ጥሪ መተላለፉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.