Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መዝመት ከሀገር ህልውና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ በተግባር ያረጋገጡበት ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግንባር እንገናኝ ባሉት መሰረት ያሳዩት ቆራጥነት በታሪክ ስንሰማው የነበረውን በተግባር በዓይናችን እንድንመለከት ያደረገ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ በሰጡት መግላጫ ፥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መዝመት ከሀገር ህልውና በላይ ምንም ነገር እንደሌለ በተግባር ያረጋገጡበት መሆኑን አስረድተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መዝመትና በግንባር ተገኝተው የቅርብ አመራር መስጠት ፥ ታላቅ ታሪካዊ ክስተት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆራጥነት በታሪክ ስንሰማው የነበረውን ብዙ ነገሮችን በተግባር በዓይናችን እንድንመለከት ያደረገ ነው ብለዋል።

የመሪው ወደ ግንባር መዝመት መላውን ህዝብ ያነሳሳ መሆኑንም አስረድተዋል።

በተለይም መላው ሰራዊቱ እና የፀጥታ ሃይሉ በከፍተኛ የውጊያ ሞራልና ወኔ ለበለጠ ድል እንዲነሳሳ ማድረጉንና በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ድል በማስመዝገብ ላይ እንዲገኝ ማድረጉን ጠቁመዋል።

አሁን ላይ ወደተሟላ የማጥቃት እርምጃ የገባውን የወገንን ጦር ክንድ መቋቋም ያቃተው የጠላት ሃይል በሚፈረጥጥበት ጊዜ ንብረት አውድሞና ዘርፎ እንደዳያመልጥ ህብረተሰቡ ተደርጅቶ ሰራዊቱን እንዲያግዝና አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድም መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.