የአማራ ሙህራን መማክርት ጉባኤ ለወገን ጦር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ሙህራን መማክርት ጉባኤ ለወገን ጦር ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ፡፡
የአማራ ሙህራን መማክርት ጉባኤ ድጋፉን ያደረገው በአዲስአበባና በውጭ ከሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ከተሰበሰበ ገንዘብ መሆኑን የጉባኤው አባልና ተወካይ አቶ ተቀባ ተባባል ተናግረዋል።
የሙህራን መማክርት ጉባኤው ለጎንደር ከተማ አስተዳደር ግምቱ ከ500ሺ ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍን በግንባር ለሚዋደቁ የቁርጥ ቀን ልጆች እንዲውል ድጋፉን አስረክቧል።
ከአንድ ሳምንት በኃላ በሁለተኛው ዙር በሁመራና ጋሸና ግንባሮች ጉባኤው 500ሺ ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የአይነት ድጋፎችን ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተወካዩ አቶ ተቀባ ተባባል ገልጸዋል።
ድጋፉ 38 ኩንታል ተምርን ያካተተ ሲሆን ÷ 513ሺህ ብር ወጪ የተደረገበት ነው ተብሏል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ ÷ ጠላትን ለማሸነፍ በሚደረገው ጥረት እንደዚህ አይነት ድጋፎች ከፍተኛ እገዛ ስላላቸው በተናጠከረ መንገድ መቀጠል አለባቸው ብለዋል
በቀጣይም የተጠናከረ ድጋፍ ለሀገር ክብር ለሚዋደቁ የቁርጥ ቀን ጀግኖች እንደሚደረግ ጉባኤው አስታውቋል።
በክብረወሰን ኑሩ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!