Fana: At a Speed of Life!

ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን መደበኛ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን መደበኛ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተመላከተ፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከሲቪል ስርቪስ ኮሚሽንና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በቀጣይ የሚያደርጉትን የስራ እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ሃገሪቱ አሁን ያለችበትን ቀውስ አስታውሰው÷ የህልውና አደጋውን በአጭር ጊዜ ለመቀልበስ መደበኛ ስራዎች እየተሰሩ ትግሉን ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የለውጥ ኃይሎች ከሚባሉት ሴክተሮች ዉስጥ የሲቪል ሰርቪስ ሴክተር ዋናው በመሆኑ ለውጡ በትክክል ስር እንዲሰድ ትልቅ ሚና ሊጫወት የሚችል ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከክልሎች ጋር ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ጨምሮ ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የተቀላጠፈና ውጤታማ አገልግሎት ከመስጠት አኳያ በዘርፉ ጠንካራ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ÷ አገልግሎት አሠጣጥን አስመልክቶ ተገልጋዩ አገልግሎት ሲቀርብለት እንዴት እንደሚጠቀም ማወቅ ስላለበት ከስድስተኛ ክፍል በላይ ያሉ ተገልጋዮች ሊገባቸዉ የሚችል የዲጅታል ክህሎት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.