Fana: At a Speed of Life!

ዘመን ባንክ ከታክስ በፊት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘመን ባንክ ዓመታዊ ትርፍ ከተለያዩ ተቀናናሾች በፊት ብር 1 ነጥብ 4 ቢሊየን መድረሱን እና የባንኩ አጠቃላይ ሐብትም 25 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሆኑን የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ገለጹ፡፡
ባንኩ ይህን ውጤት ያስመዘገበው የብድር አቅርቦቱን በማሳደግና የተበላሹ ብድሮችን ከመሰብስብ በተጨማሪ ወጪን በአግባቡ ማስተዳደር በመቻሉ ነው ተብሏል፡፡
ባንኩ የተለያዩ ተግዳሮቶች በኢኮኖሚው ላይ ያደረሱትን ጫና በመቋቋም ከፍተኛ ትርፍ ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡
አቶ ኤርሚያስ እሸቱ የባንኩ ዓመታዊ ትርፍ ከታክስ በፊት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንና ዓመታዊ ገቢው ደግሞ ከ 2 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እ.ኤ.አ በጁን 2021 መጨረሻ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 25.2 ቢሊዮን ብር የደረስ ሲሆን÷ ካለፍው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ36 ነጥብ 66 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
የተከፈለ ካፒታሉም ከብር 1ነጥብ 8 ቢሊየን በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ወደ 2 ነጥብ 749 ቢሊየን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡
በተቀማጭ ገንዘብ ረገድም ባንኩ ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ31 ነጥብ 9 በመቶ ዕድገት በማሳየት ተጨማሪ 4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል፡፡
በብድር ረገድም እንዲሁ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር 44 ነጥብ 3 በመቶ ወይንም የ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ዓመታዊ ዕድገት ማስመዝቡን፣ እንዲሁም በውጭ ምንዛሪ በኩል ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ9 ነጥብ 3 በመቶ ዕድገት መመዝገቡን ጠቅሰዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.