Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ልማት ማኅበር ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ፍጆታ አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አማራ ልማት ማኅበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማው ገዳሙ ማኅበሩ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ፍጆታ ድጋፍ ማድረጉን ገለጹ፡፡
ድጋፉ የተሰበሰበው ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ሲሆን÷ 400 ኩንታል የዳቦ ዱቄት መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገጠቁመው÷ የተሰበሰበውን የዓይነት ድጋፍ ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ማስረከባቸው ተናግረዋል፡፡
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ሌሎች አጋሮችም ድጋፉን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡
በእታገኝ መኮንን
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.