የሶማሌ ክልል የመንግስት ልዑካን ቡድን ሀርጌሳ ገባ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን ቡድን ሃርጌሳ ገባ፡፡
የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ÷ ልዑካን ቡድኑ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር በጸጥታ፣ በንግድ ትስስርና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ብለዋል፡፡
ልዑኩ የሶማሌ ክልል ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙባሽር ዲባድ ራጌ፣ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲራህማን ኢድ ጣሂር እና ሌሎች የፌደራልና የክልሉን ከፍተኛ የአመራር አካላትን ማካተቱን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!