የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዘማች ቤተሰቦች ሰብል የመሰብሰብ ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ህዳር 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ኮሌጅና የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል የመሰብሰብ ሥራ በማከናወን አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰበሀ ገብርኤል ቀበሌ እንዲሁም በብላጅግ እና ሌሎች የተለያዩ አካባቢዎች የሰብል መሰብሰብ ሥራው መከናወኑን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቀጣይም የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!