የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደርገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን- ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደርገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን” ሲሉ የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድን ተቀብለው በጽህፈት ቤታቸው አነጋግረዋል።
በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የንግድ ትስስር በማሳደግ የጋራ ብልጽግና ማረጋገጥ በሚሉ አጀንዳዎች ላይም መምከራቸው ተገልጿል።
በዚህ ወቅት አቶ ሙስጠፌ የቀጠናው የሠላም ሁኔታን በተመለከተ ከጎሮቤት ሶማሌላንድ ጋራ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች አብራርተዋል።
የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጋራ በመከላከል በአፍሪካ ቀንድ ያሉት ህዝቦች እጣ ፋንታቸው የተሳሰረ በመሆኑ በራሳቸው ጉዳይ መወሰን የሚችሉት እራሳቸው ብቻ መሆኑንም ገልጸዋል።
የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በበኩላቸው “የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለሚያደረገው የህግ ማስከበር ዘመቻ ድጋፋችንን እንገልጻለን” ብለዋል።
የበርበራ ወደብ በዩናይትድ አረብ ኢምሬቶች አስፈላጊውን የማስፋፊያ ግንባት ከተደረገበት ወዲህ ለኢትዮጵያ የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ፤ የሁለትዮሽ የንግድ ተስስሩን ለማሳደግ ዝግጅ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!