Fana: At a Speed of Life!

ጠላትን በርትታችሁ ታገሉ – በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) "በስደት መኖር ስለማይቻል እንዲሁም ሀገር ለቅቆ የትም ስለማይደረስ ጠላትን በርትታችሁ ልትታገሉ ይገባል" ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሀብተማሪያም እማኛው ተናገሩ፡፡…

አልጄሪያ ለሞሮኮ የምትልከውን ጋዝ አቋረጠች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አልጄሪያ ወደ ሞሮኮ የምትልከው ጋዝ ማቋረጧን አስታወቀች፡፡ ውሳኔው በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል፡፡ ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት የወጣ መግለጫ “ሞሮኮ ሀገራችንን እና ብሔራዊ አንድነታችንን…

ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 225 ተማሪዎች በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ በ7ኛ ዙር መርሃ-ግብሩ አስመርቋል ። ተመራቂዎቹ በመደበኛ፣ በርቀትና ተከታታይ መረሃ ግብር የሰለጠኑ ሲሆን ከመካከላቸውም 485…

በጦርነቱ የታጣውን ምርት ለማካካስ የቀውስ ወቅት ዕቅድ ይተገበራል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት የታጣውን ምርት ለማካካስና እንስሳትን ለመተካት የቀውስ ወቅት ዕቅድ እንደሚተገበር የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር…

ኤፍ ኤም ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማሰራጨት ተከለከሉ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች የውጭ አገር ፕሮግራሞችን ሊንክ አድርጎ ማስተላላፍ ከዛሬ ጀምሮ መከልከሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ በሀገር ውስጥ ፈቃድ ያልተሰጣቸው የውጭ ሀገር የሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ ባላቸው…

ቻይና የንፋስ ኃይል ማመንጫ በባህር ዳርቻዎቿ ላይ እየገነባች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ የካርበን ልቀት መጠኗን ለመቀነስ የሚያስችላትን የንፋስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተርባይኖች በባህር ዳርቻዎቿ ላይ እየገነባች መሆኑን አስታወቀች፡፡ በዚህም በቢጫ ባህር በ40 ኪሎ ሜትር ርዝመት 150 የንፋስ…

“ሜታ” – አዲሱ የፌስ ቡክ ኩባንያ ሥያሜ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፌስ ቡክ ኩባንያ ስያሜውን “ሜታ” በሚል መቀየሩን አስታወቀ፡፡ ፌስ ቡክ የኩባንያውን ስያሜ የቀየረው “ቨርችዋል ሪያሊቲ” የተባለውን አዲስ አገልግሎት እና ሌሎች ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ለተጠቃሚዎቹ ማስተዋወቅ እና ብራንዱን ማደስ በመፈለጉ ነው…

በውስጥና በውጭ የተጋረጡ ችግሮችን ለማለፍ በጋራ መቆም ያስፈልጋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር በውስጥም በውጭም እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለማለፍ በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ገለጹ፡፡ ሰብሳቢዋ አሁን ካለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር መደማመጥ፣ መነጋገርና በጋራ መቆም…

የምዕራብ ጎጃም ዞን በደሴ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ጎጃም ዞን በአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለተጠለሉ ዜጎች የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ። የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊና የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ወንድሜነህ ልየው…

የማረሚያ ቤት ሠራተኞችና ታራሚዎች ለሠራዊቱ የደም ልገሳና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የማረሚያ ቤት ሠራተኞችና ታራሚዎች በግንባር ለሚፋለመው የጸጥታ ኃይል የደም ልገሳና የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ። የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ቀፀላ ደበበ እንዳሉት፤ የህግ ታራሚዎቹ የመንግስትን የድጋፍ ጥሪ በመቀበል…