Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ብሔርን መሰረት ያደረገ ማዋከብ የለም – የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ብሔርን መሰረት ያደረገ ማዋከብ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ገለጹ። የመዲናዋ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ…

ሁዋዌ በቴክኖሎጅው ዘርፍ የትብብር ስራዎቹን የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ በኢትዮጵያ ሲያከናውናቸው የነበሩ ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ የትብብር እና የድጋፍ ስራዎችን የማጠናከር ፍላጎት እንዳለው በልዑካኑ በኩል ገልጿል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ የሁዋዌ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ልዑክ ጋር…

በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ ከጋና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከጋና ጋር አቻ ተለያይቷል። ጋናዎች በጨዋታው አንድሬ አየው ባስቆጠራት የቅጣት ምት ጎል ሲመሩ ቢቆዩም ጌታነህ ከበደ በጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ ባስቆጠራት ጎል ዋልያዎቹ አቻ ተለያይተዋል።…

የ12ኛ ክፍል ፈተና ይፈተናሉ ከተባሉ ተማሪዎች 96 ከመቶ በላይ በመፈተን ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ። የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናዎች…

ህወሓት በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች እስካሁን ከ279 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት አድርሷል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ከ279 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚበልጥ የሀብት ውድመት ማድረሱን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሃላፊ አቶ አንሙት በለጠ እንዳስታወቁት ÷ አሸባሪው በወረራ…

በመዲናዋ አከራዮች የተከራዩን መሉ መረጃ እንዲያስመዘግቡ ፖሊስ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት አከራዮች የተከራዩን መሉ መረጃ እንዲያስመዘግቡ ፖሊስ አሳስቧል፡፡ በከተማዋ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የተከራዩን መሉ መረጃ በመያዝ…

በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የሰራዊት አባላት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የጉምሩክ ኮሚሽንና የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በህልውና ዘመቻው ጉዳት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡ ድጋፉን ያደረጉት የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ…

በመጪዎቹ ሦስት ወራት የምግብ ዋጋ ቅናሽ እንደሚያሳይ ተተነበየ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የምግብ ዋጋ ቅናሽ እንደሚያሳይ መተንበዩን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው በየወሩ በሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ መሰረት የጥቅምት ወርንም ይፋ አድርጓል። በአጠቃላይ ባለፈው ወር 34 ነጥብ 8 በመቶ…

ህዝቡ ለክተት አዋጁ በሰጠው ምላሽ ድል እየተመዘገበ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ህዳር 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ ለክተት አዋጁ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ድል እያስመዘገበ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ የክተት አዋጁ ከታወጀ…

ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየተካሄደ ያለውን ሴራ ለማክሸፍ ጠንክረን እንሰራለን- የጋምቤላ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ ያለውን አሸባሪው የህወሓት ቡድንና የተላላኪዎቹን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ ጠንክረው እንደሚሰሩ የጋምቤላ ክልል የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ገለጹ፡፡ ከክልሉ የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የአመራር…