Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ። ሹመቱ ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ የጸደቀ ሲሆን፥ አቶ ሽመልስ አብዲሳም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት አቶ ሽመልስ አብዲሳ…

የሰውነት ሙቀትን የሚለይ ሮቦት ተሰራ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ተመራማሪዎች ያልተለመደና ወጣ ያለ የሰውነት ሙቀትን የሚለይ ሮቦት ሰርተዋል። አዲሱ ሮቦት ሰው በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ከተለመደው ወጣ ያለ የሰውነት ሙቀት ያለባቸውን ሰዎች መለየት የሚችልና ማንነታቸውን የሚያነብ ነው ተብሏል።…

በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የነዳጅ መያዣ ውስጥ ቁርጥራጭ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የነዳጅ መያዣ (ታንከር) ውስጥ ቁርጥራጭ ቁሳቁሶች ተገኙ። ቁርጥራጮቹ የተገኙት ለተለያዩ አየር መንገዶች ሊሰጡ በተዘጋጁ አዳዲስ የኩባንያው ምርቶች ላይ ነው ተብሏል። ሁኔታው በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን…

ማይክ ፖምፔዮ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት ቀናት ያካሄዱትን ጉብኝት አጠናቀቁ። ማይክ ፖምፔዮ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…

ያልተመጣጠነ አመጋገብ እና የአየር ንብረት ለውጥ በህጻናት ላይ ስጋት ደቅኗል – ተመድ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የንጥረ ምግብ አቅርቦት እጥረት እና የአየር ንብረት ለውጥ በሁሉም ሕፃናት ላይ ስጋት መደቀኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ከተመድ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት እና ላንሴት ሜዲካል ጆርናል የተውጣጣ ቡድን በጋራ ባወጣው ሪፖርት የስነ…

ብሪታኒያ ዝቅተኛ የሙያ ክህሎት ላላቸው ሰራተኞች ቪዛ እንደማትሰጥ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታኒያ ዝቅተኛ የሙያ ክህሎት ላላቸው ሰራተኞች ቪዛ እንደማትሰጥ አስታወቀች። ከአውሮፓ ህብረት ጋር ከፈጸመችው ፍቺ በኋላ መንግስት አዲሱን የስደተኞች እቅድ ይፋ አድርጓል። በዚህም የብሪታኒያ መንግስት አሰሪዎች በዝቅተኛ የሰራተኛ ዋጋ ላይ…

አንድነትና ሰላምን ለማረጋገጥ ክላሽና ታንክ ሳይሆን የሚያስፈልገው ልማትን ማረጋገጥ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን አንድነት እና ሰላም ለማረጋገጥ ክላሽና ታንክ ሳይሆን የሚያስፈልገው ልማትን ማረጋገጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለነዋሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።…

ማይክ ፖምፔዮ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ጋር ተወያዩ። በውይይታቸውም በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት አስፈላጊነትን በተመለከተ መምከራቸው ነው የተገለጸው።   የውጭ…