Fana: At a Speed of Life!

ከጾታዊ ጥቃት የጸዳች፣ ለሴቶችና ህጻናት የምትመች ሀገር ለመገንባት ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል- ወ/ሮ ያለም ጸጋይ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ጸጋይ ከጾታዊ ጥቃት የጸዳች፣ ለሴቶችና ህጻናት የምትመች ሀገር ለመገንባት ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል። የ16ቱ ቀን የፀረ ጾታዊ ጥቃት ንቅናቄ የመዝጊያ ፕሮግራም በዛሬው…

በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥና ተመሳሳይ የሆነ የታራሚዎች ይቅርታ አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የክልሎችንና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አሰራር፣አደረጃጀትና፣አፈፃፀም ምን እንደሚመስል በመዳሰስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥና ተመሳሳይ የሆነ የይቅርታ አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር የሚያስችል ጥናት ማካሄዱን አስታወቀ፡፡…

የአማራ ክልል የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል ባላቸው ሠራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅሬታ ምንጭ ሆነዋል ባላቸው ከ20 በላይ ሠራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ። በ2011 ዓ.ም ከአስቸኳይ ጥገና፣ ከኃይል መቆራረጥና አዳዲስ ጥያቄዎች፣ ከቅድመ ቆጣሪ ክፍያ መስተንግዶ፣ ከንብረት አያያዝና አጠቃቀም እና…

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ፓስፖርት የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ፓስፖርት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ሊተገበር ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ፓስፖርት የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ፓስፖርት ማግኘት የሚችሉበት አሰራር ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢሚግሬሽን፣ የዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡…

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በጅቡቲ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የመንግስት ልዑካን ቡድን በጅቡቲ ጉብኝት እያደረገ ነው። ልዑኩ ጅቡቲ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱላዚዝ መሃመድ አቀባበል ተደርጎለታል።…

ለሰላም ኖቤል ተሸላሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ነገ አቀባበል ስነ ስርዓት ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነገው እለት የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግ ተገለፀ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው እለት በኖርዌይ ኦስሎ ተገኝተው…

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ያሸነፉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለሰላም ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘ ነው – አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 1፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተርበ ዐቢይ አህመድ ያሸነፉት የሰላም የኖቤል ሽልማት ለሰላም ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ። የጠቅላይ ሚኒስትሩን የኖቤል ሽልማት መቀበል አስመልክቶ በአሜሪካ የኢትዮጵያ…

በኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ደስታቸውን በሰልፍ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኖርዌይ ኦስሎ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማትን በማግኘታቸው ደስታቸውን በሰልፍ ገለፁ። ኢትዮጵያዊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክትር ዐቢይ ባረፉበት ግራንድ ሆቴል ተገኝተው ነው…

ሰላም እንደ ዛፍ ችግኝ ነው፤ እንክብካቤ ይፈልጋል- ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ሰላም እንደ ዛፍ ችግኝ ነው፤ ችግኝን ተክሎ ለማሳደግ ለማሳደግ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ሰላምም ጥሩ ልብ እና እንክብካቤ ያስፈልገዋል” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ…

130 የቅማንት የማንነት ኮሚቴ አባላት በክልሉ መንግስት የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 130 የቅማንት የማንነት ኮሚቴ አባላት የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀበለው በመግባት በአካባቢው ሠላም ዙሪያ እየመከሩ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና…