ስፓርት
ሞሮኮ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሞሮኮ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡
11 ሰዓት ላይ በተካሄደው የምድብ 6 ጨዋታ ለሞሮኮ አሽራፍ ሀኪሚ እንዲሁም ለዲሞክራቲክ ኮንጎ ካቶምፓ ሙቩምፓ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡
ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያገኘቻትን የፍፁም ቅጣት ምት አጥቂው ሴድሪች ማካምቡ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ የቡድን ማጣሪያ መርሐ-ግብሮች ሲቀጥሉ÷ 2 ሰዓት ላይ ዛምቢያ ከታንዛኒያ እንዲሁም ደቡብ አፍሪካ ከናሚቢያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Read More...
ኢትዮጵያ ከኮሎምቢያ የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆነች
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ዙር ጨዋታውን ከሞሮኮ አቻው ጋር አድርጓል፡፡
ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገውን የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ በፀሐይነሽ ጁላ ጎል ሞሮኮን 1 ለ 0 ብታሸንፍም÷ በድምር ውጤት 2 ለ 1 ተሸንፋ ከኮሎምቢያው የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆናለች፡፡…
በታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በተካሄደ የታታ ሙምባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ፡፡
በሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁ ሲሆን ÷አበራሽ ምንሰዎ ፣ሙሉሃብት ፅጌ እና መድህን በጀኔ ከአንደኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ…
በአፍሪካ ዋንጫ አንጎላ ሞሪታኒያን 3 ለ 2 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አንጎላ ሞሪታኒያን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
ውጤቱን ተከትሎ አንጎላ ከቡርኪናፋሶ እኩል በአራት ነጥብ እና በአንድ ንጹሕ ግብ ምድቡን መምራት ችላለች፡፡
በአንጻሩ ሞሪታኒያ ያለምንም ነጥብ በምድብ አራት ግርጌ ላይ ተቀምጣለች፡፡
አርሰናል ክርስታል ፓላስን 5 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ክርስታል ፓላስን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ፡፡
የአርሰናልን ጎሎች ገብርዔል ማጋሌስ በ11ኛው፣ ሄንደርሰን በራሱ ጎል ላይ በ37ኛው ደቂቃ፣ ትሮሳርድ በ59ኛው እንዲሁም ገብርኤል ማርቲኔሊ በ94ኛው እና በ95ኛው ደቂቃዎች ላይ አስቆጥረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና…
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የካሜሩን አቻውን 3 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምድብ ሦስት የሚገኙት ሴኔጋል እና ካሜሩን ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኖቹ ያደረጉትን የምድብ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ÷ እስማኤል ሳር በ16ኛው፣ ሀቢብ ዲያሎ በ71ኛው እና ሳዲዮ ማኔ በ95ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፏቸው ጎሎች ሴኔጋል ድል አድርጋለች፡፡
የካሜሩንን የማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ…
ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡
በዛሬው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሞዛምቢክን 3 ለ 0 አሸንፋለች፡፡
ጎሎቹንም÷ ቤቤ፣ ያን ሜንዴስ እና ኬቪን ሌኒ አስቆጥረዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ 1 መርታቷ ይታወሳል፡፡…