ስፓርት
ላሚን ያማል የ2024 ወርቃማ ታዳጊ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የባርሴሎና እና የስፔን ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ላሚን ያማል የ2024 ወርቃማ ታዳጊ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
በጀርመን አስተናጋጅነት በተካሄደው የ2024 የአውሮፓ ዋንጫን ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያሸነፈው ያማል የውድድሩ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሽልማትንም አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ የተጫዋቹ ወኪል ጆርጌ ሜንዴዝ የ2024 የወርቃማ ታዳጊ ተጫዋች ምርጥ ወኪል በሚል ተሸልሟል፡፡
Read More...
ጓርዲዮላን ምን ነካቸው?
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የእግር ኳስ ሊቅ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ከትናንቱ ጨዋታ በኋላ ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው መቦጫጨራቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
በውድድር ዓመቱ ማንቼስተር ሲቲ እያሳየ ባለው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት ከተጫዋቹ ጋር እሰጣገባ ውስጥ የገቡት አሰልጣኙ÷ በተከታታይ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ የሥነ ልቦና ጫና…
በሻምፒየንስ ሊጉ ሊቨርፑል ከሪያል ማድሪድ የሚያድርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ 5ኛ ዙር ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲካሄዱ ሊቨርፑል እና ሪያል ማድሪድ አንፊልድ ላይ የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ የሰርቢያው ሬድ ስታር ቤልግሬድ ከጀርመኑ ስቱትጋርት እንዲሁም የኦትስሪያው ስትሩም ግራዝ ከስፔኑ ዢሮና ይጫወታሉ፡፡…
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ለመምራት የሚወዳደሩ አምስት የመጨረሻ ዕጩዎች ይፋ ሆነዋል።
በዚሁ መሠረት ከትግራይ ክልል አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም፣ ከአማራ ክልል አቶ ያየህ አዲስ፣ ከኦሮሚያ ክልል አትሌት ስለሺ ስኅን፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮ/ር ግርማ ዳባ፣ ከድሬዳዋ…
አትሌት ብዙነሽ ታደሰ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጄሪያ አቡጃ እየተካሄደ በሚገኘው 2ኛው የመላው አፍሪካ የጦር ሀይሎች ስፖርት ፌስቲቫል ኢትዮጵያን የወከለው የመቻል ስፓርት ክለብ አትሌቲክስ ቡድን ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ በጦር ውርወራ ማግኘት ችሏል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዛሬ ፍፃሜያቸውን ባገኙ የተለያዩ ውድድሮች ተጨማሪ አራት ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።
በጦር…
ዛምቢያዊቷ ባርብራ ባንዳ የዓመቱ ምርጥ ሴት የእግር ኳስ ተጫዋች ተሸላሚ ሆነች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዛምቢያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ኦርላንዶ ፕራይድ እግር ኳስ ክለብ የፊት መስመር ተጫዋች ባርብራ ባንዳ የ2024 የቢቢሲ ምርጥ ሴት እግር ኳስ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈች፡፡
የስፔን ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና የባርሴሎና አጥቂ አይታና ቦንማቲ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ የአሜሪካ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እና ሳን ዲያጎ ተከላካይ…
ባየርንሙኒክ ከፒኤስጂ እንዲሁም ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲካሄዱ ባየርንሙኒክ ከፒኤስጂ እንዲሁም ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ ስሎቫን ብራቲስላቫ ከኤሲሚላን እንዲሁም የቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ይጫወታሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ…