ስፓርት
ወልቂጤ ከነማ የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣መስከረም 14፣2015 (ኤፍ ቢሲ) ወልቂጤ ከነማ የ2015 የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ሻምፒዮን ሆኗል።
ክትፎዎቹ የዩጋንዳውን ክለብ ቡል ኤፍ ሲ 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻሉት።
በባህርዳር ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ወልቂጤ ከመመራት ተነስቶ በሳሙኤል አስፈሪ እና ጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች ማሸነፍ ችሏል።
የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ በአራት የሀገር ውስጥ ክለቦች እና በሁለት ተጋባዥ የውጭ ሀገር ክለቦች መካከል ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ ፍፃሜውን አገኝቷል።
Read More...
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የደልሂ ግማሽ ማራቶን አምባሳደር ሆነ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በህንድ ዴልሂ በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 የሚካሄደው ግማሽ ማራቶን ዓለም አቀፍ ዝግጅት አምባሳደር ሆኗል፡፡
የህንዱ የስፖርት መፅሄት የሆነው ዘ ሂንዱ እንዳስታወቀው የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊው ኃይሌ ገብረሥላሴ በፈረንጆቹ ጥቅምት 16 ቀን በሚካሄደው የቬዳንታ ደልሂ ግማሽ…
ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ 0 ለ 0 ተጠናቀቀ፡፡
አንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተካሄደ ሲሆን÷ ጨዋታው ያለምንም ግብ ተጠናቋል፡፡…
ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ከ 23 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
አንደኛ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡…
ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በመቀጠሌ ደስተኛ ነኝ – አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በመቀጠሌ ደስተኛ ነኝ ሲሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ተናገሩ፡፡
አሰልጣኙ ባሳለፍነው ዓርብ ተጨማሪ የሁለት ዓመት ውል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር መፈራረማቸውን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ በመግለጫቸው÷ እስከ መስከረም 2017…
በሲድኒ የሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ ሲድኒ በተደረገ የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵውያን አትሌቶች በፍጽም የበላይነት አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ትዕግስት ግርማ ርቀቱን 2 ሰዓት 25 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመጨረስ ወድድሩን በአንደኛነት አጠናቃለች፡፡
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ለተብርሃን ሀይላይ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ 45…
ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
ፋሲል ከነማ በዛሬው እለት በመልስ ጨዋታው 1 ለ 0 ቢሸነፍም በድምር 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ…