ስፓርት
ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉትን ጨምሮ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ሞሮኮ ከፖርቹጋል የሚያደርጉትን ጨምሮ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡
በዚሁ መሠረት ዛሬ በሚካሔድ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ የአፍሪካ ብቸኛ ተወካይ ሆና የቀረችው ሞሮኮ ከፖቹጋል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ይፋለማሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ እንግሊዝ ከፈረንሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል፡፡
ትናንት በተካሔዱ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ክሮሺያ ብራዚልን እንዲሁም አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በመለያ ምት…
Read More...
አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርጀንቲና እና ኔዘርላንድስ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በመለያ ምት 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን 90 ደቂቃ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት…
ብራዚል በክሮሺያ ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫ ተሰናበተች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗ ብራዚል በክሮሺያ በመለያ ምት ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫው ተሰናበተች፡፡
በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ብራዚል እና ክሮሺያ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም ክሮሺያ የአምስት ጊዜ የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮኗን ብራዚል በመለያ ምት 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ…
ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በተካሔዱ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ መድን እና ሀዲያ ሆሳዕና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፍዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮጵያ ቡናን ዳግም ንጉሴ በ33ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል አሸንፏል፡፡
በሌላ የ11ኛ ሣምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1…
በፕሪሚየርሊጉ የተጫዋቾች ዝውውር የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ሕዳር 29፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ የ2015 ዓ.ም አጋማሽ የተጫዋቾች ዝውውር የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆኗል፡፡
በዚህም መሰረት የውድድር አመቱ አጋማሽ ዝውውር ከታህሳስ 18 እስከ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ተሰናበቱ
አዲስ አበባ፣ህዳር 29፣2015 (ኤፍ ቢሲ) ሉዊስ ኤነሪኬ ከስፔን ብሄራዊ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸውን የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
ስፔን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ በሞሮኮ በመለያ ምት መሸንፏን ተክትሎ ነው ፌዴሬሽኑ ሉዊስ ኤነሪኬን ከብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነቱ የተሰናበተው።
አሰልጣኙ እና የቡድን አጋሮቻቸው ብሄራዊ ቡድኑን በመምራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ…
የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሣምንት ጨዋታ የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የኢትዮ ኤሌክትሪክን ጎሎች ኢብራሂም ከድር በ60ኛው እንዲሁም ናትናኤል ሰለሞን በ74ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
የአርባምንጭ ከተማን ጎሎች ደግሞ አሕመድ ሁሴን በ3ኛው እና አላዛር…