ስፓርት
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ታዛቢዎችና የጠቅላላ ጉባዔው አባላት ተገኝተዋል።
በጉባዔው መክፈቻ የ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።…
Read More...
ዋሊያዎቹ በቻን ማጣሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ ከሩዋንዳ አቻው ጋር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡
የቻን የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በታነዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በጫወታውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ…
“ማሜሎዲ ሳንዶውንስ”ን ለተቀላቀለው አቡበከር ናስር አቀባበል ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካውን ማሜሎዲ ሳንዶውንስ የተቀላቀለውን ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር አቀባበል አደረጉለት፡፡
በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አመራሮችም እንደተገኙም ነው የተመለከተው፡፡…
የኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የቻን ማጣሪያ ጨዋታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ጨዋታውን እያካሄደ ነው፡፡
የቻን የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በታነዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ በሩዋንዳ እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ ግብር አመላክቷል፡፡
ጨዋታው 10 ሰዓት ላይ የጀመረ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ ዛሬ ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡
የቻን የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በታነዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ተከላካዩ ያሬድ…
በቻምፒየንስ ሊጉ ባየርሙኒክ እና ባርሴሎና በሞት ምድብ ተገናኝተዋል
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል በዛሬው እለት ይፋ ሆኗል።
ምሽት ላይ በተካሄደው ድልድል ምድብ ሶስት የሞት ምድብ ሆኗል።
ባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና፣ ኢንተር ሚላን እና ቪክቶሪያ ፕለዘን ያገናኘው ምድብ ታላላቅ ቡድኖችን እርስ በእርስ አገናኝቷል።
በሌሎች ምድቦች በምድብ አንድ አያክስ፣ ሊቨርፑል፣ ናፖሊ እና…
ለኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ
አዲ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ፡፡
ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ጋር ለሚኖራት የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ የተላለፈ ሲሆን÷ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ነሐሴ 23 ቀን…