Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ማጣሪያ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023 የሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች የማጣሪያ ውድድር ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ዙር  የማጣሪያ ውድድር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ተደልድላለች። ኢትዮጵያ ይህን ዙር የምታልፍ ከሆነ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ አልጄሪያን የምትገጥም መሆኑን ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

አቡበከር ናሰር ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጠረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናሰር ለደቡብ አፍሪካው ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የመጀመሪያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡   በአሬና ስታዲየም በተደረገው የሰንዳውንስ እና የካይዘር ቺፍስ ጨዋታ አቡበከር በ76ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ በመግባት ነው ለክለቡ 4ኛውን ለራሱ ደግሞ የመጀመሪያውን ግብ ማስቆጠር የቻለው፡፡  …

ለአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር በስካይላይት ሆቴል ተካሄደ፡፡   በሽልማትና እውቅና መርሐ ግብር ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ እና የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት…

በሻምፒዮናው 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የጎዳና ላይ አቀባበል አየተደረገለት ነው፡፡ በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የልዑካን ቡድኑ፥ በትናንትናው ዕለት አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል…

በሻምፒዮናው 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገባ፡፡ በኮሎምቢያ ካሊ በተካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የልዑካን ቡድኑ÷ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡…

ዋልያወቹ በቻን ማጣሪያ የመጨረሻ የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያደርጉበት ቀንና ቦታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር በቻን ማጣሪያ የመጨረሻ የደርሶ መልስ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎቹን የሚያደርግበት ቀናት እና ቦታ ይፋ ሆኗል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ኢትዮጵያ ባለሜዳ የምትሆን ሲሆን÷ በዚህም ነሐሴ 20 ቀን 2014 ዓ.ም በታንዛንያ ዳሬሰላም ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ላይ ጨዋታዋን…

በሞናኮ ዳይመንድ ሊግ አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ላይ በሞናኮ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ የ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው አሸነፈች፡፡ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር አትሌት ወርቅውኃ ጌታቸው 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት አንደኛ ስትወጣ÷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ደግሞ 9 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ63…