Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በቼክ ሪፐብሊክ የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በቼክ ሪፐብሊክ ኦስትራቫ ከተማ በተካሄደ የኮንቲኔንታል ቱር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በውድድሩ አትሌት ጌትነት ዋለ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር 8 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ ከ47 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡ በዚህ ውድድር ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም የተሳተፉ ሲሆን በወንዶች በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ሳሙኤል አባተ በ3 ደቂቃ 36 ሰከንድ ከ32 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ውድድሩን 3ኛ…
Read More...

ሰበታ ከተማ አዳማ ከተማን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠና የራቀበትን ውጤት አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰበታ ከተማ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። ሰበታ ከተማ በመጀመሪያው አጋማሽ 35ኛው ደቂቃ ላይ ኦሴ ማወሌ ባስቆጣራት ብቸኛ ግብ ነው ማሸነፍ መቻሉን ከሱፐር ስፖርት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በዚህም የሰበሰበውን ነጥብ 33 በማድረስ በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ከፍ…

ሀድያ ሆሳዕና ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1ለ 0 አሸንፏል። ዛሬ ረፋድ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሀድያ ሆሳዕናን እና ቅዱስ ጊዮርጊስን አገናኝቷል፡፡ በጨዋታው ሀድያ ሆሳዕና ቅዱስ ጊዮርጊስን 1ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የማሸነፊያና ብቸኛዋን ግብ ደግሞ…

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬ ዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬ ዳዋ ከተማ ፋሲል ከነማን 3 ለ 1 አሸንፏል። በዚህም ከፕሪሚየር ሊጉ  የመውረድ ስጋት ያለበት ድሬ ዳዋ ከተማ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችሏል። የድሬ ዳዋን ማሸነፊያ ግቦች ሪችሞንድ አዶንጎ ፣ኢታሙና ኬሙይኔ እና ሰዒድ ሀሰን በራሱ ላይ ሲያስቆጥሩ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ሙጂብ…

በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባጅፋርና ባህርዳር ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ረፋድ ላይ አንድ ጨዋታ ተካሄዷል፡፡ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጅማ አባጅፋርን ከባህርዳር ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና 3ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ አቡበከር ናስር ለኢትዮጵያ ቡና ሶስቱንም ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ የሰራ ሲሆን፤ በሲዳማ ቡና በኩል መሃሪ መና፣ ማማዬ ሲዲቤ እና ይገዙ ቦጋለ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር አቻ መለያየት ችለዋል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ…

አቡበከር ናስር የፕሪምየር ሊጉን የግብ አግቢነት ሪከርድን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አቡበከር ናስር በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል የማስቆጠር ሪከርድን ሰብሯል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ላይ 9ኛ፣ 36ኛው እና 90ኛው ደቂቃ ላይ ግብ አስቆጥሮ የውድድር ዘመኑ ጎሎቹን ቁጥር 27 አድርሷል፡፡ በዚህም ከወዲሁ በጌታነህ ከበደ በ2009 ተይዞ የነበረውን በአንድ የውድድር ዘመን…