Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴር 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት ከ1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብሰቧል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በመድረኩ እንዳነሱት÷ በበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባበሰብ ሂደቱን የሚያሳደጉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።

የገቢ አቅምን ለማሳደግ የታክስ መሰረቶችን የማስፋት፣ የታክስ አስተዳደርና ታክስ ፖሊሲን የማሻሻል እንዲሁም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አገልግሎት አሰጣጥን ተግባራዊ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 28 ትሪሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢታቀድም በግማሽ ዓመቱ አፈጻጸም ዕቅዱን ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ከፍ በማድረግ መከለሱን አስታውሰዋል።

በዚህም በዕቅዱ መሰረት በተሰራው ስራ 1 ነጥብ 518 ትሪሊየን ብር ገቢ በመሰብሰብ የዕቅዱን 101 ነጥብ 24 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የሀገር ውስጥ ታክስ፣ የውጭ ንግድ፣ ቀረጥና ታክስ በበጀት ዓመቱ የተሰበሰበው ገቢ የተገኘባቸው ዘርፎች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የበጀት ዓመቱ ገቢ ከ2017 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ68 ነጥብ 69 በመቶ እድገት ማሳየቱም ተመላክቷል፡፡

በዳዊት ጎሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.